በኦሮሞ ፕሮቴስት ተሰብሮ የነበረው የወያኔ ወገብ

 

Fayisa Lelisaበኦሮሞ ፕሮቴስት ተሰብሮ የነበረው የወያኔ ወገብ አሁን ደግሞ በፈይሳ ሌሊሳ የወያኔ አንገት ተሰብሮል ። የኢትዮጵያ መንግስት ለዘመናት ስጨቁን አና ድምጹን ሲያፍን የነበረው የኦሮሞ ህዝብን ዛሬ ባላሰበውና ባልገመተው መንገድ ድንገት አንገቱ አና ማጅራቱ በመመታቱ ኩፉኛ ታሞል ። ምንም አንኴ መች አንደምሞቱ ባይታወቅም ለዚህ አና በመሰልሎች አደጋዎች መደሃኒት አልተገኛለትም ። ለዚህ በሽታዎች መድሃኒት አለመገኛቱ ብቻ ሳይሆን ከእንግዲህ ወዲህ በምን አይነት በሽታ መጠቃት እንደምችሉ ፈጽሞ መገመት ወደማይችሉበት ደረጃ ደርሶል ።

ጀግናው እና ውድ የኦሮሞ የቁርጥ ቀን የሆናው ፈይሳ ለሊሳ በወሰደው እና ባሰያው የኦሮሞ ተቃውሞ እንዲሁም ለወገኑ ባሳየው ተቆርቋሪነት ፣ የወገኖቹ መታሰር ፣ የወገኖቹ መሞት ፣ የወገኖች ደም መፍሰስ ፣ የወገኖች አጥንት መሰበር ፣ የወገኖች ከቄኤው መፈናቀል ፣ የወገኖቹ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መሆን ፣ የወገኖች ንብረት እና ሀብት መዘረፍ ያሳሰበው ፈይሳ ፣ ለራሱ ብቻ ተመቻችተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር እንደምሰቀቅቀው ስለተረደው በነጻነት እና በችግር ከወገኖቹ ጋር ለመኖር ወስኖ የኦሮሞን ነጻነትን ትግል ተቀላቅሏል ።

ይህ በእንዲህ እያለ ለዘመናት ጆሮዉን ዘግታው እና ቆልፎው የነበረው የአለም ማህበረሰብ ዛሬ ሳይወድ በግዱ ጆሮዉን ለኦሮሞ እንድሰጥ አስችሎታል ። ከዛም አልፎ ለሃያ አምስት አመታት የኢትዮጵያ መንግስትን አንደ ልዩ እና ድሞክራቲክ መንግስት ሲያዩት ለነበረው የኣሜሪካው እና የአውሮፓ መንግስታት ትልቅ ውርደት ነው ። ይበልጥ ለአሜሪከው ፕሬዚዳንት ባረክ ኦበማ ትልቅ ዉርደት ነው። ምክኛቱም ይህን ያህል ንጽሃን የኦሮሞ ህዝብ በያ እስር ቤት እየተማቀቃ እያሌ ፣ በመቶዎች ሺ የምቆጠር የኦሮሞ ህዝን እየተገደላ እያሌ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ምንም አይነት መግለጫ ሳይሰጥ እና በተቃራኒው ኢትዮጵያ ሰላም የሰፈናበት ማለቱ ለእሱ ዉርደት ነው ። ከዛ ብዙም ሳይቆይ የኦሮሞ ህዝብ ትግል በኣዲስ መልኩ ተጀምሮ እናሆ እስከ ዛሬ የወያኔን የጀርባ አጥንት እና የኣንገትን አጥንትን በመሰባበር ይገኛል ።

በመቀጠለም የኣሜሪካ መንግስት ፣ የኣዉሮፓ መንግስት ፣ የሀበሻ ህዝብ ፣ እና የኢትዮጵያ መንግስት ሊረዱ የሚገባቸው በኢትዮጵያ አይደለም በኢስት ኣፊሪካ ሰላም የሚባል ነገር አይኖርም የኦሮሞ ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ። የኦሮሞ ጥያቄ ስመለስ ፣ የኦሮሞ ህዝብ የስልጣን ባለቤት ሲሆን ፣ የኦሮሞ ህዝብ የኣገሩ ባለቤት ሲሆን ፣ የኦሮሞ ህዝን ራስን በራስ ማስተዳደር ስልጣን ሲኖረው እና በቋንቋው ባህሉ ማሰደግ ስልጣን ስኖረው ብቻ ነው ኢትዮጵያም ሆና ኢስት ኣፊሪካ እንደ አገር ሆኖ የሚቀጥሉት የሚኖሩት ።

አለማየሁ ጥላሁን

Leave a Reply

%d bloggers like this: