ወያኔ አልሚ ኦሮሚያ አዉዳሚ እና ጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ የለም የተባለዉ

 

gonderዘጠኝ ወር ያስቆጠረዉ የኦሮሚያ ተቃዋሚ እንቅስቃሴ ከግዜ ወደ ጊዜ ስልቱን እና ጥንካሬዉን ጨምሮ መላዉን ኦሮሚያ እንደ እሳት እየተቀጣጣላ ያለው ያዳረሰዉ የባለቤትነት ጥያቄ፣ የኣልገዛም ጥያቄ፣ የመብትና የፍህ ጥያቄ እንጂ ያአዉዳሚነት ጥያቄ ኣይደለም። ወያኔ አልሚና ኦሮሚያ ኣዉዳሚ ተብለዉ እና እንደ ሆና ተደርጎ በወያኔ አፈ ቀላጤና የመንግስት ኮሚኒኬሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሰዒድ የቀረበዉ ዉንጀላ የመንግስታቸዉ አጭበሪባሪናታቸዉን የሚያንጸባርቅ እና ከሀቅ የራቃ ነዉ። የወያኔ መንግስት ፊቱን በጨዉ ታጥቦ መዋሽት እና ዉሸት ከእናቱ ማህጻን እያለ ነበር ። ይህ ዉሸትና ዉንጀለዉ ለኦሮሞ ህዝብ አድስ ነገር ኣይደለም ። የሚገርመዉና የሚያሰዝነዉ ግን የኦሮሞዉን ህዝብ እንደ ህዝብ ሳይቆጥሩ በደል ስያደርጉበት እና ስበዘብዙ ቆይተዉ አገር በኣንድነት እንዳላቸዉ ነው የሚታሰበዉ። የሚገርመዉ ግን ዛሬ ገባቸዉም ኣልገባቸዉ አንድ ቀን የምጸጸቱበት ጊዜ እና ዘማናት ሩቅ አይሆንም። ጭቆናዉና ብዝበዛዉ ቀርቶ በአሳሳቢ ሁኔታ ዕለት ከዕለት የኦሮሞዉን ንጹሃን ዜጎችን ነፍስ እያጠፉ ይገኛሉ። ይህ ማለት የትግሬዉ ነፍስ ይገዳል የኦሮሞው ነፍስ አይገድም እንደ ማለት ነው። Black life matter's እንደሚባለዉ የኦሮሞዉ ( Oromo Life matter’s ወደሚባለው ደረጃ ሳይለወጥ አይቀሬ ነው።

በተያያዘው የወያኔ ፕሮፖጋንዳ አራማጅ እና የአማራ ክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንደተናገሩት የተደራጀ ጥያቄ ስላልቀረበ በጎንደር ሠላማዊ ሰልፍ አይኖርም ብለው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተው ነበር። ምስሉ እና ቪድዮ ላይ እንደተመለከታቹህ የጎንደር ህዝብ ከቤት ሳይቀር ወደ አደባባይ ወቶ ከእንግዲህ በኃላ ወያኔን ፍቃድ መጠየቅ ይቅርና በወያኔ አንገዛም ፣ አማራ ኩሩ ነው፣ የህወሃት አገዛዝ ይብቃ፣ ከእንግድህ በወያኔ አንገዛም እና የመሳሰሉትን መፈክሮችን ሲያሰሙ ዉሎል። የጎንደሬዉ ህዝብ ከእንግድህ ለወያኔዉ እንደማይተኛ ፣ የኣማራው ህዝብ እንደ ባድማው ሁሉ ድል እንደሚያደርግ ፣ አማረ ውስት ታስራው ያሉት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድፈቱ ማስጠንቃቂያ ጭምር ለመንግስት መልዕክት አስተላልፎል።

በዚህ ተቃዉሞ ሰልፍ ዉስጥ አማራው የበላይናቱን አሳይቶል ። አንድም ሰው ሳይነካ እና ሳይጎዳ ሰልፈኞቹ በሰላም ወደ በታቸው ገብቶል። በኦሮሚያ ዉስጥ እንደዚህ አይናት ሰልፍ ቢካሄድ ኖሮ ምን ያህል ሰው በወያኔ አጋዚ ወታደር እንደሚገደል ጥያቄ የለዉም ። ኦሮሚያን ይህን ያህል ልደፍሩና ልሳፈጡት የቻሉበት ምክንያት መልሱ አንድ እና አንድ ነው። ይህም ሰው ይቅርና እንስሳ እንኳን በአንድ አይን ያማያት እና ከራሱ አስበልጦ ሰዉን የማክበር እንደ ድሞክራሲ ስለሚያየዉ ይህም ሰባዐዊናቱ በለሎቹ በበታችናት እና የመናቅን ስሜትን ፈጥሮላቸወል። ይህ መቆም አለበት ቅድሚያ ለራስ ነው ባይ ነኝ።

 

አለማያሁ ጥላሁን

Leave a Reply

%d bloggers like this: